የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በብዛት በመሰመራት ቀዳሚ እንደሆኑ ተገለጸ
17:07 24.04.2025 (የተሻሻለ: 17:24 24.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በብዛት በመሰመራት ቀዳሚ እንደሆኑ ተገለጸ
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከተሳቡ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ውስጥ ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ከፍተኛውን ድርሻ እንድሚይዝ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ከ12 ሃገራት የመጡ የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እያፈሰሱ እንደሆነ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ ሀገራቱ ከታች የተዘረዘሩት ናቸው፦
ቻይና - 114
ህንድ -7
ዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች - 4
ካናዳ - 3
ኔዘርላንድ - 3
አሜሪካ - 2
ቱርክ - 2
ሳዑዲ አረቢያ -1
ባንግላዲሽ -1
ሱዳን -1
ኒውዝላንድ -1
ሞርሸስ -1
በስርጭት ደረጃ ሲታይ በአዲስ አበባ 76፣ በኦሮማያ 48፣ በአማራ 13፣ በትግራይ 4፣ በሲዳማ 3 እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያና አፋር እያንዳንዳቸው አንድ የውጭ ባለሀብት ወደ ሥራ አስገብተዋል።
ወደ ማምረት ከተሸጋገሩት ውስጥ የምግብና መጠጥ፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት እና የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደ ቅደም ተከተላቸው ደረጃ መያዝቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አሳይቷል፡፡