በኢትዮጵያ በ72 ከተሞች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማሻሻያ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ
16:24 24.04.2025 (የተሻሻለ: 17:14 24.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ በ72 ከተሞች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማሻሻያ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ በ72 ከተሞች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማሻሻያ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ
አስራ አንድ ክልሎችን የሚያካትተው ይሄ ፕሮጀክት በሁለት ምዕራፎች የሚተገበር ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ 34 ሁለተኛው ደግሞ ተጨማሪ 38 ከተሞችን ይሸፍናል።
ማሻሻያው የሀገሪቱ የኃይል ስርዓቶችን ዘመናዊ ማድረግ እና በአካባቢ ደረጃ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ የታሰበው ስትራቴጂ አካል ነው ተብሏል።
የፕሮጀክት ኃይል አቅርቦት ጥራትና አስተማማኝነትን ማሻሻል፣ የትራንስፎርመር አቅምን ማሳደግ፣ የኃይል ኪሳራን መቀነስ እና የቮልቴጅ መለዋወጥን ማረጋጋት የእቅዱ ትኩረት እንደሆነም ተገልጿል።
በዚህም 6 ሺህ 183 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የመካከለኛ ቮልቴጅ ማከፋፈያ መስመሮች ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው የተገለጸ ሲሆን የ5 ሺህ 569 ማከፋፈያ ትራንስፎርመሮችን አቅም ያሳድጋል ተብሏል።