ከአዲስ አበባ የሚመነጩ ቆሻሻዎች ወደ ታዳሽ ኃይል ሊቀየሩ ነው
16:05 24.04.2025 (የተሻሻለ: 16:24 24.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከአዲስ አበባ የሚመነጩ ቆሻሻዎች ወደ ታዳሽ ኃይል ሊቀየሩ ነው
ከአዲስ አበባ መንጭተው ረጲ አካባቢ የሚጣሉ ቆሻሻዎችን ወደ ኢኮ ፓርክነት የሚቀይር እና የኃይል አማራጭን በማስፋት ተጨማሪ ገቢ ያስገኛል የተባለ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈርሟል፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው በቻይና ሻንዥን ኢነርጂ ግሩፕ፣ የቻይና ብሔራዊ ኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ድርጅት እና በጀርመኑ ኮቬናንት ኢንጅነሪንግ ድርጅት መካከል ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ከተማዋን ውብ እና ፅዱ እንዲሁም ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የሚያግዝ ነው መባሉን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።