ጊቤ ሶስት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከእቅዱ በላይ ኃይል ማመንጨቱ ተገለፀ
11:51 24.04.2025 (የተሻሻለ: 12:14 24.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጊቤ ሶስት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከእቅዱ በላይ ኃይል ማመንጨቱ ተገለፀ
በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 4 ሺ 725 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ፤ 5 ሺ 436 ጊጋ ዋት ኃይል ማምረት ተችሏል።
ይህም ከእቅዱ የ15.4 በመቶ ብልጫ እንዳለው የኃይል ማመንጫው የኦፕሬሽን ኃላፊ ደጀኔ ጉታ አስታውቀዋል፡፡
አፈፃፀሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ189.65 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም የ3.61 በመቶ ብልጫ አለው።
የጊቤ 3 ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በ18 ማመንጫ ጣቢያዎች ከተመረተው የ21 ሺ 299 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ የ25.5 በመቶ ድርሻ በመያዝ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ተከትሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።