ሩሲያ የአፍሪካ ወዳጆቿን ወረርሽኝን የመዋጋት አቅም የሚያግዝ ሰፊ ፕሮግራም እንደጀመረች ፑቲን ገለፁ
19:45 23.04.2025 (የተሻሻለ: 20:04 23.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ የአፍሪካ ወዳጆቿን ወረርሽኝን የመዋጋት አቅም የሚያግዝ ሰፊ ፕሮግራም እንደጀመረች ፑቲን ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የአፍሪካ ወዳጆቿን ወረርሽኝን የመዋጋት አቅም የሚያግዝ ሰፊ ፕሮግራም እንደጀመረች ፑቲን ገለፁ
ፑቲን በጤና አጠባበቅ እና ድንገተኛ ወረርሽኞች ምላሽ አሰጣጥ ላይ ባተኮረው የመጀመሪያው የሩሲያ-አፍሪካ ዓለም አቀፍ ልምምድ ላይ ባደረጉት ገለጻ የወረርሽኝ መከላከያ ፕሮግራሙ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፦
🟠 ከ150 በላይ የአፍሪካ ባለሙያዎችን እንዳሰለጠነ፣
🟠 በደርዘን በሚቆጠሩ አደገኛ ኢንፌክሽኖች ላይ የጋራ ምርምር ማካሄዱን እንዲሁም
🟠 ስድስት ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎችን ወደ አፍሪካ ሀገራት መላኩን ገልጸዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ ኢትዮጵያ ውስጥ በሩሲያ፣ በ15 የአፍሪካ ሀገራት እና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል የሚደረገው የጋራ ልምምድ የእውቀት ልውውጥ እና ተላላፊ የበሽታ ወረርሽኞችን ለመከላከል ጠቃሚ መድረክ እንደሆነ አመልክተዋል።