የሩሲያ ድጋፍ በጥቅሟ ላይ የተመረኮዘ አይደለም ሲሉ የሩሲያ የሸማቾች መብት እና የዜጎች ደህንነት ጥበቃ ኤጀንሲ ኃላፊ ተናገሩ
18:46 23.04.2025 (የተሻሻለ: 19:04 23.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ድጋፍ በጥቅሟ ላይ የተመረኮዘ አይደለም ሲሉ የሩሲያ የሸማቾች መብት እና የዜጎች ደህንነት ጥበቃ ኤጀንሲ ኃላፊ ተናገሩ
ኃላፊዋ ዶክተር አና ፖፖቫ ይሄን ያሉት የሩሲያ መንግሥት በዛሬው እለት ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ያደረገውን ድጋፍ አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት መግለጫ ነው። ኤጀንሲው ከተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ ድጋፍ በተጨማሪ ለድንገተኛ ወረርሽኝ እና ለጤና ቀውስ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስምምነት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል።
"ሩሲያ ከአፍሪካ አህጉር ጋር ወዳጃዊ፣ የመደጋገፍ እና በጋራ እርዳታ ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አላት። ይህ ደግሞ ድጋፍ በሚሰጠው አካል ጥቅም ላይ ከተመረኮዘው የሌሎች ሀገራት የእርዳታ አሰጣጥ ጋር ፍጹም የተለየ ነው" ብለዋል።
ኃላፊዋ አክለውም የሩሲያ የላብራቶሪ እርዳታ "ሀገራት የራሳቸውን ባዮሎጂ ነክ ስጋቶች መቋቋም አለባቸው" በሚለው መርህ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ተናግረዋል።