በኢትዮጵያ 1.6 ሚሊየን ሄክታር ላይ የተዘራ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት መሰብሰቡን ግብርና ሚኒስቴር ገለፀ
16:05 23.04.2025 (የተሻሻለ: 16:44 23.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ 1.6 ሚሊየን ሄክታር ላይ የተዘራ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት መሰብሰቡን ግብርና ሚኒስቴር ገለፀ
በዚህ ዓመት ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 172 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እንደነበር የገለፁት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኢሳያስ ለማ፤ እስካሁን 3.5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን አስታውቀዋል፡፡
አክለውም በበልግ አብቃይ አካባቢዎች በስፋት ወደ ሥራ መገባቱንና 3.7 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን 98 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ኃላፊው የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አርሶ አደሮች በመኸር፣ በበልግና በበጋ መስኖ ዓመቱን ሙሉ እንዲያመርቱ እየተሠራ መሆኑን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡