በሶማሊያ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ የሽብር ጥቃት በማክሸፍ ያሰለጠናቸውን ሙያተኞች አስመረቀ
15:43 23.04.2025 (የተሻሻለ: 16:04 23.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሶማሊያ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ የሽብር ጥቃት በማክሸፍ ያሰለጠናቸውን ሙያተኞች አስመረቀ
ስልጠናው በሶማሊያ በድጋፍ ሰጪነት ተሰማርተው ለሚገኙ የምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር አባላት እንደተሰጠ ተገልጿል። ከተባበሩት መንግሥታት የፈንጂ እርምጃ አገልግሎት ጋር በመተባበር የተሰጠው ስልጠና የንድፈ-ሀሳብ እና የተግባር ስልጠናን ያካተተ እንደነበር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።
የሴክተር አራት ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሹመት ጠለለው ሙያተኞቹ ከስልጠናው ባገኙት እውቀት የተሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
"በየጊዜው ቴክኖሎጂዎች እየተሻሻሉ በመጡ ቁጥር ብዙ አማራጮች ይኖራሉ። ከግዳጅ ቀጣናው ጋር ተያይዞ አልሻባብ በዋናነት የሚጠቀምባቸውን ፈንጆች በመለየት እና ፍተሻዎችን በማድረግ ጉዳት ሳያደርሱ ማስወገድ ቀዳሚው ተግባር ነው" ሲሉ አሳስበዋል።