ፑቲን በ2024 ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ድሮኖች ለሩሲያ ወታደሮች መላካቸውን ተናገሩ
14:55 23.04.2025 (የተሻሻለ: 15:14 23.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፑቲን በ2024 ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ድሮኖች ለሩሲያ ወታደሮች መላካቸውን ተናገሩ
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ፦
🟠 ሩሲያ በ2024 የጦር መሳሪያ ምርቷን ከእጥፍ በላይ አሳድጋለች።
🟠 የሩሲያ ወታደሮች በ2024 ከ4 ሺህ በላይ ብረት ለበስ የጦር መሳሪያዎችን፣ 180 የውጊያ አውሮፕላኖችን እና ሄሊኮፕተሮችን ተረክበዋል።
አክለውም የተለያዩ ሀገራት ጦሮች እና የጦር መሣሪያ አምራቾች የሩሲያን በራስ አቅም ጦርነትን የማካሄድ ልምድ እያጠኑ ነው ብለዋል።
በዚህ ዓመት የሩሲያ ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ከ2024 የበለጠ ትልቅ ግቦች እንዳሉትም መሪው አስታውቀዋል።
"ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን በማዳበር የወደፊት ግጭቶችን መተንበይ አለብን" ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ ዙሪያ ያሉ ዓለም አቀፍ አዝማሚያዎችንም ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል ብለዋል።