የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአማራ ክልል የባህር ዳር ሪጅን ከ15ሺ በላይ አዲስ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አደረገ
13:32 23.04.2025 (የተሻሻለ: 13:54 23.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአማራ ክልል የባህር ዳር ሪጅን ከ15ሺ በላይ አዲስ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አደረገ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባህር ዳር ሪጅን ባለፉት ዘጠኝ ወራት አዳዲስ ደንበኞችን ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ 63 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 134 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታና 175 ትራንስፎርመር የማስቀመጥ ሥራ አከናውኗል።
ከመኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎች በተጨማሪ የትምህርት፣ የውሃ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አገልግሎቱ ጨምሮ ገልጿል።
በተጨማሪም በመልሶ ግንባታ በሠራቸው ተጨማሪ ተግባራት የኃይል መቆራረጥ ያለባቸውን አካባቢዎች ችግር መቅረፍ መቻሉን አስታውቋል።