የሩሲያ መንግሥት ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ ለኢትዮጵያ ለገሰ
12:55 23.04.2025 (የተሻሻለ: 16:44 23.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ መንግሥት ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ ለኢትዮጵያ ለገሰ
ላብራቶሪውን የሩሲያ የሸማቾች መብት እና የዜጎች ደህንነት ጥበቃ ኤጀንሲ ኃላፊ ዶክተር አና ፖፖቫ ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አስረክበዋል።
ሩሲያ ሰር የሆነው ይህ ላብራቶሪ "በሽታን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል" አስተዋጽኦ ያደርጋል ሲሉ ኃላፊዋ ዶክተር አና ፖፖቫ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል።
ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪው የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት በማጠናከር በተለይም ተላላፊ በሽታዎችን የመቋቋም አቅም በማጎልበት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ማለታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
የሕክምና መሳሪያው በአንድ ጊዜ 300 በሽታዎችን የመለየት አቅም እንዳለውም ጠቁመዋል።