የጃፓኑ ቶዮ በኢትዮጵያ የገነባው የሶላር ማመረቻ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ
11:57 23.04.2025 (የተሻሻለ: 12:34 23.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጃፓኑ ቶዮ በኢትዮጵያ የገነባው የሶላር ማመረቻ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ
በሐዋሳ ከተማ በስልሳ ሚሊዮን ዶላር የተገነባው ፋብሪካ አሁን ላይ የማምረት አቅሙ 2 ጊጋዋት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ኩባንያው በመጪው ነሐሴ የማምረት አቅሙን ወደ 4 ጊጋዋት እንደሚያሳድግ አስታውቋል።
በሚያዚያ ወር መጨረሻ ኩባንያው ከ80 ሜጋዋት በላይ የፀሐይ ሴሎችን ወደ ውጭ ይላካል ተብሎ እንደሚጠበቅ አሳውቋል።
የቶዮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጁንሴይ ሪዩ "በገበያው ላይ ባየነው ጠንካራ ፍላጎት በጣም ደስተኞች ነን፡፡ በኢትዮጵያ የ2 ጊጋዋት የማስፋፊያ ሥራ ለመተግበር በትጋት እየሠራን ነው" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በቬትናም የቶዮ ኩባንያ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ማምረቻ ፋብሪካን በጎበኙበት ወቅት ኩባንያው በኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍ በስፋት እንዲሳተፍ ማበረታታቸው ይታወሳል።