የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለካሜሩን ሃጅ ተጓዦች የተቀላጠፍ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ገለፀ
11:22 23.04.2025 (የተሻሻለ: 11:44 23.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለካሜሩን ሃጅ ተጓዦች የተቀላጠፍ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ገለፀ
በካሜሩን የግዛት አስተዳደር ሚኒስትርና የሃጅ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ጎብኝቷል።
ልዑኩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ጋር ፍሬያማ ውይይት እንዳካሄደ አየር መንገዱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በውይይቱ ወቅት አየር መንገዱ ከካሜሩን ለሚመጡ የሃጅ ተጓዦች አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል። በተጨማሪም ወደ ያውንዴ እና ዱአላ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ የበለጠ አጠናከሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።