የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሠልጣኞችን አስመረቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሠልጣኞችን አስመረቀ
የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሠልጣኞችን አስመረቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.04.2025
ሰብስክራይብ

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሠልጣኞችን አስመረቀ

ኤጀንሲው በሁለተኛ ዙር የኮደርስ ሥልጠና 127 ሠልጣኞችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በአጠቃላይ 367 ባለሙያዎቹ የኮደርስ ስልጠና እንደወሰዱ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ በቴክኖሎጂ ክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል ለማፍራት አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

አክለውም የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ንቅናቄ ከዚህ አኳያ ሚናው አይተኬ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ተቋማት ሠራተኞቻቸው ሥልጠናውን እንዲወስዱ የሚያደርጉትን ጥረት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንደሚያግዝም አረጋግጠዋል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0