ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሳበችው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት 2.4 በመቶ እድገት እንዳስመዘገበ ተገለጸ
14:15 22.04.2025 (የተሻሻለ: 14:34 22.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሳበችው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት 2.4 በመቶ እድገት እንዳስመዘገበ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን እንደገለፁት ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ እንደ ፋይናንስ እና ቴሌኮም እና ሌሎችም የኢንቨስትመንት ዘርፎች መከፈታቸው ለእድገቱ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል።
ኮሚሽነሩ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደተናገሩት የጅምላና ችርቻሮ ወጪና ገቢ ንግድ መከፈቱን ተከትሎ ለ40 የውጭ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን እንዲሁም ለ36 ባለሃብቶች ፍቃዱን ለመስጠት በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠናም 11 የሚሆኑ ባለሃብቶች እንደገቡና አንዳንዶች ሸቀጦችን ጭምር እያመጡ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
@sputnik_ethiopia