ኢትዮጵያ አዲሱን የልማት ባንክ ለመቀላቀል የብሪክስ አባላትን ድጋፍ ማግኘቷን አስታወቀች
13:33 22.04.2025 (የተሻሻለ: 13:54 22.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ አዲሱን የልማት ባንክ ለመቀላቀል የብሪክስ አባላትን ድጋፍ ማግኘቷን አስታወቀች
ባንኩን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረቧን እና በቅርቡም ሂደቶቹን አልፋ እንደምተቀላቀል ያላቸውን ተስፋ ያሳወቁት በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልኡልሰገድ ታደሰ ናቸው።
አምባሳደሩ አክለውም ኢትዮጵያ ባንኩን ከተላቀለች የትኩረት አቅጣጫዎቿ ባንኩ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዘርፎች መካከል ግብርና፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ ይሆናሉ ብለዋል።
አምባሳደሩ ከቲቪ ብሪክስ ጋር በነበራቸው ቃለ-መጠየቅ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላትን አቅም የዘረዘሩ ሲሆን ብሪክስ የተቀላቀለችበት አንዱ አላማ የኢኮኖሚ ትስስሯን ለማጠናከር መሆኑን እና ለዚህም የቱሪዝም ኢንደስትሪው አንዱ መንገድ መሆኑን ገልፀዋል።
@sputnik_ethiopia