ሩሲያ ሁልጊዜም የተኩስ አቁምን በተመለከ አዎንታዊ አመለካከት አላት ፤ የትንሳኤው የተኩስ አቁም ተነሳሽነት ጥሩ ማሳያ ነው በማለት ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ተናገሩ
ሩሲያ ሁልጊዜም የተኩስ አቁምን በተመለከ አዎንታዊ አመለካከት አላት ፤ የትንሳኤው የተኩስ አቁም ተነሳሽነት ጥሩ ማሳያ ነው በማለት ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ተናገሩ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት በመግለጫቸው ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች ፦
⏺ ሞስኮ የዩክሬን ወገን ለሰላም ተነሳሽነት አዎንታዊ አመለካከት አለው ብላ ተስፋ ታደርጋለች፤
⏺ ሩሲያ የትንሳኤ የተኩስ አቁም ተሞክሮ ላይ ትንተና ማድረግ ይኖርባታል፤
⏺ የዩክሬን የጦር ኃይሎች የተኩስ አቁሙን 5 ሺህ ጊዜ ጥሰዋል፤ ነገር ግን በአጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ቀንሰው ነበር ፤
⏺ ሩሲያ በሲቪል ዒላማዎች ላይ ጥቃቶችን ለማስቆም የቀረቡትን ሀሳቦች በመተንተን ምላሽ ትሰጣለች፤
⏺ ኪየቭ የሲቪል ተቋማትን ለወታደራዊ ዓላማዎች ይጠቀማል ፤ ለምሳሌ ፣ ከውጭ ሀገራት ተቆጣጣሪዎች ጋር በመሆን ኦዴሳ ውስጥ የሚሳኤል ሙከራ ሂደቶችን ለማደራጀት ሞክሯል ፤
⏺ በሱሚ የሩሲያ ጥቃት በሲቪል ተቋም ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም ዒላማ የተደረጉትን እና ለህገወጥ ድርጊቶቻቸው ተገቢውን ክፍያ የተቀበሉት በቦታው የነበሩ የጦር ወንጀለኞች ናቸው፤
ቀደም ሲል የሩሲያ ጦር በሁለት እስክንድር-ኤም ሚሳኤሎች ጥቃቶችን ማድረሱ ይታወሳል ፤ ዒላማው በሱሚ ከተማ የዩክሬን ጦር አዛዦች መሰብሰቢያ ቦታ ነበር ። በጥቃቱ ከ60 በላይ ወታደሮች መገደላቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
@sputnik_ethiopia