የሩሲያ እና የሱዳን ኩባንያዎች በነዳጅ ምርት ዘርፍ አብረው ለመስራት ተስማሙ
15:10 21.04.2025 (የተሻሻለ: 15:44 21.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ እና የሱዳን ኩባንያዎች በነዳጅ ምርት ዘርፍ አብረው ለመስራት ተስማሙ
የመግባቢያ እና የትብብር ስምምነቱ በሩሲያዎቹ አል ራሲ ኢንተርናሽናል ሰርቪስ እና ዛሩቤዝኔፍት ድርጅቶች ከፍተኛ ተወካዩች እና በሱዳኑ ባሻየር ኦይል ፒፕላይንስ ድርጅት ተወካዩች መካከል ተፈርሟል። በፊርማ ሥነ-ሥረዓቱ ወቅት የሩሲያ ኤምባሲ ልዑካን በስፍራው መገኘታቸውን የሱዳን ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሁለቱ ወገኖች አክለውም በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፦
⏺ የመጨረሻ ስምምነት ማዘጋጀት፣
⏺ ከሱዳፔት ጋር አጋርነት መመስረት እና
⏺ ከሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር በነዳጅ ፍለጋ እና ምርት አገልግሎቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ።
@sputnik_ethiopia