ሱዳን በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ አስመልክቶ በለንደን የተካሄደውን ጉባኤ አወገዘች
14:40 21.04.2025 (የተሻሻለ: 15:14 21.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሱዳን በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ አስመልክቶ በለንደን የተካሄደውን ጉባኤ አወገዘች
"በሱዳን ያለውን ህጋዊ መንግስት ያላካተተ ሀገሪቷን የተመለከተ ኮንፈረንስ ማካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለን እናስባለን" ሲሉ በሩሲያ የሱዳን አምባሳደር ሞሃመድ ኤልጋዛሊ ኤልቲጋኒ ሲራግ ለስፑትኒክ ተናተናግረዋል።
ዲፕሎማቱ "በግጭቱ ውስጥ ያሉ ወገኖች" ተብለው የሱዳን ይፋዊ ባለሥልጣናት እና የፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ በእኩል መጠራታቸውን አውገዘዋል። አክለውም አረመኔያዊ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ የታጠቁ ቡድኖችን ህጋዊ አድርጎ መሳል ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ሚያዝያ ሰባት በለንደን የተካሄደው ጉባኤ የአረብ ሀገራት ባለመስማማታቸው ምክንያት የጋራ መግለጫ ሳይሰጥበት መጠናቀቁን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
@sputnik_ethiopia