የአፍሪካ መሪዎች በሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን በመግለፅ ለሰጡት አገልግሎት ምሥጋና አቀረቡ
14:13 21.04.2025 (የተሻሻለ: 14:34 21.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ መሪዎች በሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን በመግለፅ ለሰጡት አገልግሎት ምሥጋና አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ መሪዎች በሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን በመግለፅ ለሰጡት አገልግሎት ምሥጋና አቀረቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፦ "ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን፤ የርህራሄ፣ ትህትና እና የሰው ልጆች አገልግሎት አሻራቸው ትውልዶችን የሚያነሳሳ ይሁን።"
ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ፦ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ሞት ለካቶሊክ ምዕመናን እና ለክርስቲያኑ ዓለም ትልቅ ጉዳት ነው ሲሉ ገልፀው “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጌታን፣ ቤተ-ክርስቲያንን እና የሰውን ልጅ በማገልገል ይታወሳሉ” ብለዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ፦ አቡነ ፍራንሲስ "የዘመናችን ታላቅ የሞራል ድምጽ እና ለሰላም፣ ፍትህ፣ ርህራሄ እና ሰብዓዊ ክብር ጽኑ ተሟጋች" ናቸው በማለት “ከአፍሪካ አህጉር ጋር የነበራቸውን ጥሩ ግንኙነት፣ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ እንደነበሩ፣ ሰላምና ዕርቅን የሚደግፉ መሆናቸውን አንስተዋል።
@sputnik_ethiopia