ክሬምሊን ዩክሬን የፋሢካ ተኩስ አቁም ስምምነትን እንደጣሰች የሚያሳዩ መረጃዎችን ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ
13:25 21.04.2025 (የተሻሻለ: 13:54 21.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱክሬምሊን ዩክሬን የፋሢካ ተኩስ አቁም ስምምነትን እንደጣሰች የሚያሳዩ መረጃዎችን ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ክሬምሊን ዩክሬን የፋሢካ ተኩስ አቁም ስምምነትን እንደጣሰች የሚያሳዩ መረጃዎችን ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ
ማስረጃው ማወቅ ለሚፈልጉ ወገኖች በሙሉ እንደሚቀርብ የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ቃል አቀባይ ሰኞ እለት ተናግረዋል።
ሚያዚያ 11 ቀን በቭላድሚር ፑቲን የታወጀው የትንሣኤ ተኩስ አቁም ሚያዝያ 13 (በሞስኮ ሰዓት) እኩለ ሌሊት ላይ አብቅቷል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በኪዬቭ ኃይሎች 4 ሺህ 900 የተኩስ አቁም ጥሰት መፈጸሙን ሰኞ እለት አስታውቋል።
የዲሚትሪ ፔስኮቭ ተጨማሪ መግለጫዎች፡-
🟠 የትንሣኤ የተኩስ አቁም ፕሬዝዳንት ፑቲን በራሳቸው ተነሳሽነት ያወጁት ነበር።
🟠 ለሩሲያ ስጋት የሚፈጥር በመሆኑ ዩክሬን የኔቶ አባል መሆን የለበትም።
🟠 ዋሽንግተን በተለያዩ ግዜያት የዩክሬን የኔቶ አባልነት የማይቻል መሆኑን መግለጿ ከሞስኮ አቋም ጋር የሚጣጣም ነው።
🟠 ሩሲያ እና ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን ጉዳይ የጀመሩት ግኑኝነት ውጤት ያስገኛል ብላ ሞስኮ ተስፋ ታደርጋለች።
🟠 ሩሲያ የዩክሬንን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ዝግጁ ነች።
🟠 የዩክሬን ሰላም ሂደት በአደባባይ ሊከናወን አይገባም። የመረጃ ፍሰት በጥንቃቄ መያዝ አለበት።
@sputnik_ethiopia