ቬይትናም ከአፍሪካ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደበር ትጠቀማለች ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ተናገሩ
12:56 21.04.2025 (የተሻሻለ: 13:54 21.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቬይትናም ከአፍሪካ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደበር ትጠቀማለች ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቬይትናም ከአፍሪካ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደበር ትጠቀማለች ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው ሣምንት በቬይትናም ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አሥመልክቶ ሚኒስትሩ ለገሠ ቱሉ በሰጡት ማብራሪያ፤ የቬትናም ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ እንዲሁም ከአፍሪካ ጋር የመወዳጀት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም በአጠቃላይ በተደረጉ ውይይቶች በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በትምህርት አብሮ ለመሥራት እና ኢትዮጵያን የአፍሪካ መግቢያ በር አድርጎ ለመጠቀም ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩ ተንጸባርቋል ብለዋል።
በቅርቡ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቬይትናምን ከአፍሪካ ለማገናኘት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል ማለታቸውን ጠቅሶ ሚኒስትሩ የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።
@sputnik_ethiopia