ኢትዮጵያ እና ኬንያ የሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ
11:40 21.04.2025 (የተሻሻለ: 12:24 21.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ
ይህ ስምምነት የመጣው ከሁለት ዓመታት ድርድር መሆኑ ተገልጿል። ሀገራቱ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ ስር የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ የኢትዮጵያ የድንበር ንግድ ዞን ከሞያሌ በ50 ኪሎ ሜትር እንዲሁም የኬንያ ደግሞ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚወሰን ነው እንደሆነ ተዘግቧል።
ነጋዴዎችም በጋራ በተስማሙበት የምርት ዝርዝር መሰረት እስከ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የንግድ ልውውጥ በወር እስከ አራት ጊዜ ድረስ ማካሄድ ይችላሉ።
@sputnik_ethiopia