ሶማሊያ ከ40 በላይ የዳኢሽ አሸባሪዎችን መግደሏን አስታወቀች
18:50 20.04.2025 (የተሻሻለ: 19:14 20.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሶማሊያ ከ40 በላይ የዳኢሽ አሸባሪዎችን መግደሏን አስታወቀች
የተቀናጀ ወታደራዊ ዘመቻ በቶጋ ሚራሌ እና በባሪ ክልል (ፑንትላንድ) አካባቢ በሚገኙ አሸባሪዎች ላይ መካሄዱን የሶማሊያው የዜና ወኪል ሶና ዘግቧል።
የጸጥታ ሃይሎች ቀደም ሲል የዳኢሽ* አጋር በሆነው የአልሸባብ * ቡድን ተይዘዉ የነበሩ ስትራቴጂካዊ የጦር ማዘዣዎችን እና ቁልፍ ቦታዎችን መልሰው መቆጣጠራቸው ተነግሯል።
ቶጋ ሚራሌ "ከቡድኑ የመጨረሻ መደበቂያ ቦታዎች አንዱ ነበር ፤ ይህ ውጊያ እነሱን ለማጥፋት እየተደረገ ባለው ዘመቻ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው" ሲሉ የኦፕሬሽን ሂላክ ቃል አቀባይ ጀነራል ሞሀመድ ሞሀሙድ ፋአዲጎ ተናግረዋል።
* በሩሲያ እና በበርካታ ሀገሮች የታገዱ አሸባሪ ድርጅቶች።
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
