በናይጄሪያ የቤንዩ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ማለቱን የግዛቲቱ አስተዳዳሪ አስታወቁ
16:13 20.04.2025 (የተሻሻለ: 16:34 20.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበናይጄሪያ የቤንዩ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ማለቱን የግዛቲቱ አስተዳዳሪ አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በናይጄሪያ የቤንዩ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ማለቱን የግዛቲቱ አስተዳዳሪ አስታወቁ
በትላንትናው ዕለት በናይጄሪያ ጠመንጃ የታጠቁ የከብት አርቢዎች ባደረሱት ጥቃት 17 መሞታቸውን የናይጄሪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
"እስካሁን በአንድ ሌሊት ብቻ 56 ሰዎች ስለመሞታቸው እየተነጋገርን ነው። ይህ እጅግ አሳዛኝ ነው" በማለት የአካባቢው አስተዳዳሪ ሃያሲንት አሊያ መናገራቸውን የናይጄሪያ የዜና ወኪል ዘግበዋል።
ሐሙስ እና አርብ ምሽት የተፈፀመ ጥቃት የፀጥታ ኃይሎች በአከባቢው እንዲሰማሩ ምክንያት ሆኗል። አስተዳዳሪው በአካባቢው የሚገኙ በኃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሱ የአንድ ብሄር አባላት የሆኑ ታጣቂ ከብት አርቢዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ፍለጋው በመቀጠሉ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሏል።
ይህ ጥቃት የተፈፀመው ባለፈው ሰኞ በፕላቶ ግዛት በሁለት መንደሮች ላይ ያልታወቁ ሰዎች በፈፀሙት ጥቃት 50 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
@sputnik_ethiopia