የዩክሬን እግር ተከትላ ሞልዶቫ ከሩሲያ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና ባህላዊ ግንኙነት ለማቋረጥ አቅዳለች ሲል የብራዚሉ ጋዜጠኛ ተናገረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዩክሬን እግር ተከትላ ሞልዶቫ ከሩሲያ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና ባህላዊ ግንኙነት ለማቋረጥ አቅዳለች ሲል የብራዚሉ ጋዜጠኛ ተናገረ
የዩክሬን እግር ተከትላ ሞልዶቫ ከሩሲያ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና ባህላዊ ግንኙነት ለማቋረጥ አቅዳለች ሲል የብራዚሉ ጋዜጠኛ ተናገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.04.2025
ሰብስክራይብ

የዩክሬን እግር ተከትላ ሞልዶቫ ከሩሲያ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና ባህላዊ ግንኙነት ለማቋረጥ አቅዳለች ሲል የብራዚሉ ጋዜጠኛ ተናገረ

ብራዚላዊው ጋዜጠኛ ሉካስ ሌይሮዝ የሞልዶቫ ሊቀ ጳጳስ ማርኬል ወደ እየሩሳሌም እንዳይሄዱ የተጣለባቸውን ክልከላ አስመልክቶ ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት "የሞልዶቫ መንግሥት ከሩሲያ ጋር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ግኑኝነት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ ለማጥፋት ይፈልጋል" ብሏል።

ዩክሬን እንዳደረገችው የሞልዶቫ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን ጨምሮ ከሩሲያ ጋር የተገናኙ ተቋማትን እና ምልክቶችን ኢላማ ያደርጋሉ ሲል ጋዜጠኛው ተናግሯል።

"ኦርቶዶክስ የሩሲያዊ ማንነት መሠረታዊ ገጽታ በመሆኑ የሞልዶቫ መንግሥት የሞስኮ ፓትርያርክ አካል በሆነችው የሞልዶቫ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል" ሲል ጠቁሟል።

በዚህም ባለሥልጣናቱ የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዩን የሞልዶቫ ሕዝብ ባሕላዊና ሐይማኖታዊ ፍላጎት እየናቁ ነው ብሏል።

"ሞልዶቫ የዩክሬንን መስመር መርጣለች። የአውሮፓ ሕብረትነሰ በቶሎ የመቀላቀል እና ሞስኮን ውድቅ የማድረግ አጀንዳ" ሲል ሌይሮዝ አብራርቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0