ፑቲን የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች፡-
17:32 19.04.2025 (የተሻሻለ: 17:54 19.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፑቲን የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች፡-
🟠 የተኩስ አቁሙ ከሚያዚያ 11 ቀን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ሚያዚያ 14 ቀን ከጠዋቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይቆያል።
🟠 በፋሲካ የተኩስ አቁም ወቅት ሁሉም ወታደራዊ እርምጃዎች መቆም አለባቸው። ሆንም የሩሲያ ወታደሮች የተኩስ አቁሙን ጥሰት እና የጠላት ትንኮሳዎችን ለመመከት ዝግጁ መሆን አለባቸው።
🟠 የተኩስ አቁሙ ሂደት የኪዬቭ አገዛዝ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎት እና ዝግጁነት እንዳለው የሚታይበት ይሆናል።
🟠 ሩሲያ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን ግጭት በሰላም እንዲፈታ የሚያሳዩትን ፍላጎት በበጎው ትቀበላላች።
🟠 የኪዬቭ አገዛዝ በኃይል ተቋማት ላይ ጥቃት ለማቆም የተደረሰውን ስምምነት ከ100 ጊዜ በላይ ጥሷል።
🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ለመጪው የትንሳኤ በዓል የኦርቶዶክስ ወደታደሮችን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
🟠 ፑቲን የሩሲያ ጦር አዛዥ ጌራሲሞቭ የሀገሪቱ የኩርስክ ክልል ግዛት ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነጻ ሲወጣ እንዲያስታወቁ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
@sputnik_ethiopia