የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.04.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

መሪዎቹ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ፦

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

"እንኳን ለክርስቶስ ትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ይህ ቅዱስ የበዓለ ትንሣኤ ዕለት የደስታ የፍስሐ እና የመልካምነት ቀን ነው። በዓሉን በፍቅር፣ በሰላምና በመተሳሰብ እናክብር ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

"ለኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚተጉ ብዙዎች ናቸው። የሕማማቱ ጊዜ እያለፈ ነው። አሁን ዓርብ ወደ ማታ ላይ ነን። ከጸጥታው ቀን በኋላ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይመጣል። ትንሣኤው ከእሥራኤል ለዓለም እንደተገለጠው ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ለዓለም ትገለጣለች።"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

"የኢትዮጵያ ትንሣኤ በኢትዮጵያ ማንሠራራት ተጀምሯል። ጩኸቱ እያለፈ ነው። ጨለማው እየነጋ ነው። ሤራው እየተበጣጠሰ ነው። ሁሉንም ወደ ኋላዋ እየተወችው ነው። የኢትዮጵያ ጸጋ ለዓለም እየተገለጠ ነው። በጲላጦስ ዐደባባይ በኢትዮጵያ ላይ ሲጮኹ የነበሩ ሁሉ፣ እጃቸውን በአፋቸው ይጭናሉ።"

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመተሳሰብ፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን።"

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0