በሞልዶቫ ጳጳስ ላይ የተፈፀመው ድርጊት በምስራቅ አውሮፓ እና ሌሎችም አካባቢዎች የኦርቶዶክስ ክርስትናን ተፅዕኖ ለመቀነስ ከሚደረገው ጥረት ጋር የተያያዘ ነው ሲል ኢትዮጵያዊው ዘማሪ ተናገረ
14:47 19.04.2025 (የተሻሻለ: 15:04 19.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሞልዶቫ ጳጳስ ላይ የተፈፀመው ድርጊት በምስራቅ አውሮፓ እና ሌሎችም አካባቢዎች የኦርቶዶክስ ክርስትናን ተፅዕኖ ለመቀነስ ከሚደረገው ጥረት ጋር የተያያዘ ነው ሲል ኢትዮጵያዊው ዘማሪ ተናገረ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሞልዶቫ ጳጳስ ላይ የተፈፀመው ድርጊት በምስራቅ አውሮፓ እና ሌሎችም አካባቢዎች የኦርቶዶክስ ክርስትናን ተፅዕኖ ለመቀነስ ከሚደረገው ጥረት ጋር የተያያዘ ነው ሲል ኢትዮጵያዊው ዘማሪ ተናገረ
የሞልዶቫ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ለፋሲካ ወደ እየሩሳሌም እንዳይጓዙ መከልከላቸውን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየቱን የሰጠው ጋዜጠኛ እና የኦርቶዶክስ ዘማሪ ሲኖዶስ ተስፋይ፤ የቅዱስ ብርሃን ሥነ-ሥርዓት በኦርቶዶክስ ክርስትና ትልቅ ቀን እንደሆነ እና ክልከላው ከተለመደው የኦርቶዶክስ እምነት እሴቶች መሸሽን የሚያመለክት ነው ብሏል።
"ጳጳሱ በሐይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓተ እንዳይገኙ መከልከል አሉታዊ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው። በእርግጠኝነት ለፖለቲካ ወይም የርዕዮተ ዓለም ምክንያቶች የተደረገ ነው። እርምጃው የሕዝቦችን፣ የአማኞችን እና የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን መብት የሚጥስ ነው" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
አክሎም ክልከላው ሰፋ ያለ ስትራቴጂ አካል ነው ብሏል።
"በሞልዶቫ ብቻ ሳይሆን፤ በምስራቅ አውሮፓ እና ሌሎችም አካባቢዎች የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ቁጥር የመቀነስ ስትራቴጂ ነው። በሞልዶቫ እንዲሁም በምስራቅ አውሮፓ ለኦርቶዶክስ ክርስትና አመቺ ያልሆኑ ሆኔታዎች መብዛታቸው በጣም አሳሳቢ ነው" ሲል ጨምሮ ገልጿል።
ሲኖዶስ ተስፋይ ሁኔታው ችላ ሊባል እንደማይገባም አስገንዝቧል።
"በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ተቃውሟቸውን እያሰሙ እንደሆነ አይቻለሁ። ይህ አግባብ ነው። አንድ ሆነን በቤተ-ክርስቲያኗ ላይ ተፅዕኖ እንዳይደረግ ማረጋገጥ" አለብን ሲል አፅንኦት ሰጥቷል።
@sputnik_ethiopia