በሞልዶቫ 'አዲሷን ፀረ-ሩሲያ' ሀገር ለመፍጠር ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው ሲሉ የአውሮፓ ምሑራን ተናገሩ
13:41 19.04.2025 (የተሻሻለ: 14:04 19.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሞልዶቫ 'አዲሷን ፀረ-ሩሲያ' ሀገር ለመፍጠር ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው ሲሉ የአውሮፓ ምሑራን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሞልዶቫ 'አዲሷን ፀረ-ሩሲያ' ሀገር ለመፍጠር ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው ሲሉ የአውሮፓ ምሑራን ተናገሩ
ምሑራኑ የሞልዶቫ ሊቀ ጳጳስ ማርኬል ለቅዱስ ጧፍ ሥነ-ሥርዓት ወደ እየሩሳሌም እንዳይጓዙ ሁለት ግዜ እገዳ መጣሉን በተመለከተ ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት የሞልዶቫን መንግሥት "ሐይማኖታዊ አፈና እና የጂኦፖለቲካ እርምጃ" ነቅፈዋል።
ምሑራኑ በየግላቸው የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦
▪ቭላድሚር ዲሚትሪዬቪች፦ በቤተ-ክርስቲያን ፖለቲካ መስክ የተሠማሩ የሰርቢያ ምሁር፣
"በሞልዶቫ የማያ ሳንዱ አገዛዝ የወሰዳቸው የጭቆና እርምጃዎች የቀድሞዋን የሶቪየት ሪፐብሊክ አካል ልክ እንደ ዩክሬን ወደ ፀረ-ሩሲያ ሀገር ለመቀየር ያለመ ነው"
▪ሁዋን አንቶኒዮ አጊላር የስፔን የጂኦፖለቲካ ተቋም ዳይሬክተር፦
"ሐይማኖታዊ ነፃነት ተገድቧል። ይህንንም ወደ ውጭ ሀገር እንዳይጓዙ በተከለከሉት የሞልዶቫ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ተወካዮች እያየን ነው። ... ይህ ሁሉ ውሸት ነው። በሞልዶቫመሰ ቢሆን በአውሮፓ ዴሞክራሲ የለም።"
▪የጣሊያን ዓለም አቀፍ ትንተና ተቋም ፕሬዝዳንት ቲቤሪዮ ግራዚያኒ፦
"የሞልዶቫ ባለሥልጣናት ባሕላዊ፣ ሐይማኖታዊ እና የብሔር ልዩነቶችን ለጂኦፖሊቲካዊ ፍላጎቶቻቸው የሚጠቀሙት የአውሮፓ ሕብረት በሀገሪቱ መንግሥት ላይ ባለው ተጽዕኖ ምክንያትና ከሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ባህላዊ ቅርበት ያላቸውን ሕዝቦች ለመጉዳት ነው።"
@sputnik_ethiopia