ሩዋንዳ የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ ወታደሮች ከምስራቅ ኮንጎ በግዛቷ በኩል እንዲወጡ ለማመቻቸት ተስማማች
11:06 19.04.2025 (የተሻሻለ: 11:24 19.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩዋንዳ የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ ወታደሮች ከምስራቅ ኮንጎ በግዛቷ በኩል እንዲወጡ ለማመቻቸት ተስማማች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩዋንዳ የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ ወታደሮች ከምስራቅ ኮንጎ በግዛቷ በኩል እንዲወጡ ለማመቻቸት ተስማማች
በሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ጎማ የሚገኙት የሳድክ ወታደሮች ወደ ታንዛኒያ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ሶስት የዲፕሎማሲ ምንጮች ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።
ወታደሮች በሩዋንዳ በኩል በሚጓዙበት ወቅት ለደህንነት ሲባል የጦር መሳሪያዎቻቸው ታሽገው እንደሚቆዩ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል።
የኮንጎ እና የሩዋንዳ መንግሥታት እንዲሁም የሳድክ አባል ሀገራት ስለ ወታደሮቹ መውጣት እስካሁን የሰጡት አስተያየት የለም።
የሳድክ ሰላም አስከባሪ ኃይል የኮንጎ ተልዕኮ እንደሚቋረጥ እና በሀገሪቱ የሚገኙት ወታደሮች ቀስ በቀስ መውጣት እንደሚጀምሩ ቀጣናዊው ኃይል በመጋቢት ወር አስታውቆ ነበር።
@sputnik_ethiopia