የአሜሪካና ኢራን ሁለተኛ ዙር የኒውክሌር ድርድር በዛሬው እለት ይጀመራል
09:56 19.04.2025 (የተሻሻለ: 10:14 19.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካና ኢራን ሁለተኛ ዙር የኒውክሌር ድርድር በዛሬው እለት ይጀመራል
በቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ የሚደረገው ድርድር በጣሊያን ሮም ይካሄዳል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ የኢራንን ልዑክ የሚመሩ ሲሆን የአሜሪካ የልዑካን ቡድን በመካከለኛው ምስራቅ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ይመራል።
ድርድሩ ባለፈው ቅዳሜ በኦማን ዋና ከተማ ሙስካት የመጀመሪያው ዙር ድርድር ከተካሄደ በኋላ የመጣ ነው። ኦማን በሁለተኛው ዙርም አደራዳሪነቷን የምቀጥል ሲሆን ጣሊያን አስተናጋጅ ሀገር በመሆን ትሳተፋለች።
ምስሉ አራግቺ በዛሬው እለት ወደ ሮም ሲጓዙ ያሳያል።
@sputnik_ethiopia

© telegram sputnik_ethiopia
/