በአሜሪካ እና ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች የኢራን ተገቢ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
14:56 18.04.2025 (የተሻሻለ: 15:14 18.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአሜሪካ እና ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች የኢራን ተገቢ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአሜሪካ እና ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች የኢራን ተገቢ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚከተሉትን ተጨማሪ አስተያየቶች ሰጥተዋል፦
ሩሲያ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል በኢራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችን ለማገዝ ዝግጁ ናት።
ላቭሮቭ ከኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ስለ ኢራን የኒውክሌር ስምምነት ተወያይተዋል። ሩሲያ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የሚደረገውን ውይይት በበጎው ትቀበላለች።
ኢራን በኒውክሌር ጦር መሳሪያ እገዳ ስምምነት ማዕቀፍ ከአሜሪካ ጋር በኒውክሌር መርሃ-ግብሯ ዙሪያ ለመስማማት ዝግጁ ናት።
ሩሲያ ከኢራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ጋር ያልተገናኙ ጉዳዮችን በአሜሪካ-ኢራን ምክክር ውስጥ ለማካተት የሚደረጉ ሙከራዎችን "በስጋት" ትመለከታለች።
@sputnik_ethiopia