ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ ፣ ክፍል 6፡ ካርል ሜይ ፡ የሂትለር ስነ-ፅሁፋዊ መካሪ

ሰብስክራይብ

ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ ፣ ክፍል 6፡ ካርል ሜይ ፡ የሂትለር ስነ-ፅሁፋዊ መካሪ

“ሂትለር ስለ አሜሪካ እና ህንድ ጦርነቶች እንዴት አወቀ? ነጭ ሰፋሪዎች ከነባር አሜሪካውያን ተወላጆች ጋር ያደረጉትን ትግል እንደ ጀብድ ቁልጭ አድርጎ በልብወለድ መልክ ከጻፈው ከጀርመናዊው ጸሐፊ ከካርል ሜይ ነው ፡፡” ሲሉ ከስፑትኒክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ጸኃፊው ኢጎር ያኮቭሌቭ ተናገሩ፡፡

እንደ ያኮቭሌቭ ገለጻ እነዚህ የጀብድ ታሪኮች ወጣቱ ሂትለር ነባር ወይም አሜሪካዊ ተወላጅ ጀግኖች ምንም ያህል መልካም ቢሆኑ “ነጮች ሁሉን ቻይ ናቸው ፤ እናም የበታች ዘሮችን ማጥፋትም እጣ ፋንታቸው ነው” ብሎ እንዲያስብ አድርገውታል፡፡ ነገር ግን፣ ይህ የተጣመመ ድምዳሜ የራሱ የሂትለር እንጂ፤ ካርል ሜይ ሃሳቡን በስራው ውስጥ ፈፅሞ ገልፆት አያውቅም ፡፡

ስፑትኒክ ብቻ በተከታታይ በሚያቀርበው በዚህ ቪዲዮም ፣ የታሪክ ጸኃፊዉና የናዚዝም አመጣጥና አነሳስ ታሪክ አጥኚው ፣ የጀርመናዊው ጻኃፊ ስራዎች በወደፊቱን የናዚ መሪ ሂትለር ላይ የጥላቻ አስተሳሰቦችን እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደሩ አብራርተዋል፡፡

@sputnik_ethiopia

App | Follow us on X

አዳዲስ ዜናዎች
0