ኢትዮጵያ እና ኬንያ በድንበር ከተሞች አካባቢ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት ተስማሙ
12:27 18.04.2025 (የተሻሻለ: 12:44 18.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በድንበር ከተሞች አካባቢ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት ተስማሙ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ኬንያ ፓወር
በትብብር መሥራት በሚችሉበት መንገድ ዙሪያ በኬንያ ናይሮቢ ውይይት አካሂደዋል።
የታሪፍ ድርድር፣ ፍትሐዊ እና ቀጣይነት ያለው ድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ማኖር የውይይቱ ትኩረት እንደነበር ተገልጿል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በኬንያ ባሉ የድንበር ከተሞች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
@sputnik_ethiopia