ኢትዮጵያ ወደ ሩሲያ የምትልከውን ቡና ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
11:28 18.04.2025 (የተሻሻለ: 11:44 18.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ወደ ሩሲያ የምትልከውን ቡና ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ ከሩሲያው ሜይ የቡና ኤክስፖርተር ጋር ተወያይተዋል።
ኩባንያው ፋሃም ከተባለ የኢትዮጵያ ቡና ላኪ ድርጅት ቡና እንደሚገዛ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ኩባንያው ባለፉት አምስት ዓመታት ከኢትዮጵያ የሚያስገባው ቡና መጠን እንደጨመረና በየወሩ በአማካኝ 10 ኮንቴይነር ቡና እንደሚገዛ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በሩሲያ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሀገሪቱን ቡና በሩሲያ ለማስተዋወቅና ገበያውንም ለማስፋት ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ወደ ሩሲያ የምትልከውን ቡና ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ