የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅቡልነት አሽቆልቁሎ 42 በመቶ ደረሷል ተባለ
20:19 17.04.2025 (የተሻሻለ: 20:34 17.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅቡልነት አሽቆልቁሎ 42 በመቶ ደረሷል ተባለ
ዘ ኢኮኖሚስት እና ዩጎቭ ያካሄዱት የሕዝብ አስተያየት ጥናት 52 በመቶ ምላሽ ሰጪዎች ለትራምፕ የእስካሁን አፈጻጸም አሉታዊ አመለካከት እንዳላቸው አሳይቷል።
በተመሳሳይ በሕዝብ አስተያየቱ መሠረት በጥናቱ የተሳተፉ 35 በመቶ ሴቶች ትራምፕን ሲቃወሙ፤ 49 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ፕሬዝዳንቱን ይደግፋሉ።
ከሚያዚያ 5 እስከ 7 በተደረገው ጥናት 1 ሺህ 512 ሰዎች ተሳትፈዋል።
ዎል ስትሪት ጆርናል በቅርቡ አካሂዶት በነበረው የሕዝብ አስተያየት መስጫ የትራምፕ ቅቡልነት 46 በመቶ እንደነበር ገልጿል።
@sputnik_ethiopia