ሩሲያ በኢትዮጵያ የተለያዩ የትብብር ዘርፎች ለመሳተፍ እንደምትፈልግ ገለፀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ በኢትዮጵያ የተለያዩ የትብብር ዘርፎች ለመሳተፍ እንደምትፈልግ ገለፀች
ሩሲያ በኢትዮጵያ የተለያዩ የትብብር ዘርፎች ለመሳተፍ እንደምትፈልግ ገለፀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.04.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ በኢትዮጵያ የተለያዩ የትብብር ዘርፎች ለመሳተፍ እንደምትፈልግ ገለፀች

ይህ የተገለጸው በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ገነት ተሾመ የሩሲያ ፌዴሬሽን የፕሮጀክት ቢሮ ከሆነው የስትራቴጂክ ተነሳሽነቶች ኤጀንሲ የዓለም አቀፍ ግኑኝነቶች ኃላፊ ሚካኤል ኡሪዬቪች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ኃላፊው ኤጄንሲው በኢትዮጵያ ሊያካሂዳቸው ስላቀዳቸው ፕሮጀክቶች ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ርካሽ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ምቹ ባሕልና የወጣት ኃይል አላት ያሉት ኃላፊው፤ ኤጀንሲው በፋርማሱቲካል፣ በግብርና፣ በኃይል ማስተላለፊያና በዲጂታል አገልግሎት ዘርፍ መሳተፍ እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በሰው አልባ አውሮፕላን፣ ሥነ-ምህዳር፣ የሳይበር ደህንነትና ባዮቴክኖሎጂ በመሳሰሉ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር የልምድ ልውውጥ ማካሄድ እንደሚፈልግ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋር ለማግኘት ኤምባሲው ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

አምባሰደር ገነት በበኩላቸው ኤጀንሲው በኢትዮጵያ ሊያከናውናቸው ላቀዳቸው ሁሉም ተነሳሽነቶችና ፕሮጀክቶች መንግሥት ለመተባበር ዝግጁ እንደሆነ መግለጻቸውን ሞስኮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0