ኳታር በመካከለኛው ምስራቅ ቁልፍ የሩሲያ አጋር ሀገር ናት ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኳታር በመካከለኛው ምስራቅ ቁልፍ የሩሲያ አጋር ሀገር ናት ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ
ኳታር በመካከለኛው ምስራቅ ቁልፍ የሩሲያ አጋር ሀገር ናት ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.04.2025
ሰብስክራይብ

ኳታር በመካከለኛው ምስራቅ ቁልፍ የሩሲያ አጋር ሀገር ናት ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ

ፑቲን ከኳታር ኤሚር ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በክሬምሊን ካደረጉት ውይይት በኋላ የተነሱ ተጨማሪ ነጥቦች፦

  በሩሲያ እና አሜሪካ መካከል የሚደረገው ንግግር በኳታር ሊካሄድ ይችላል። በጉዳዩ ዙሪያ ግልፅ ውይይት አልተደረገም።

ሩሲያ እና ኳታር በነዳጅ ዘርፍ ጨምሮ በርካታ የሚጠበቁ የጋራ ፕሮጀክቶች አሏቸው ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።

  ኳታር ከሩሲያ ጋር ባላት ግንኙነት ደስተኛ እንደሆነች የገለፁት የኳታር አሚር፤ በቀጣይ ውይይት የሚደረግባቸው እና የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች እና ሃሳቦች እንዳሉ ጠቁመዋል።

  ሩሲያ እና ኳታር በትራንስፖርት ዘርፍ ውጤታማ በሆነ መንገድ ትብብር እያደረጉ ነው።

የእስራኤል-ፍልስጤም ግጭት

ኳታር የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭትን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች እንደሆነ ፑቲን አንስተዋል።

  ግጭቱን በዘላቂነት መፍታት የሚቻለው በሁለት መንግሥታት መርህ መሠረት ብቻ ነው ሲሉ የሩሲያው መሪ ተናግረዋል።

ሶሪያ

ፑቲን ሩሲያ ሶሪያን እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር የማስቀጠል ፍላጎት አላት ብለዋል።

ፑቲን በንግግራቸው የኳታር አሚር ስለ ሶሪያ እና ለሀገሪቱ ስለሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያነሱ ሀሳብ አቅርበዋል።

የኳታር አሚር ቀደም ሲል ከሶሪያው መሪ ጋር በነበራቸው ግኑኝነት ከሩሲያ እና ኳታር ጋር ትብብር ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0