በኢትዮጵያ 40 የውጭ ባለሃብቶች ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማውጣታቸው ተነገረ
12:14 17.04.2025 (የተሻሻለ: 12:34 17.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ 40 የውጭ ባለሃብቶች ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማውጣታቸው ተነገረ
የሀገሪቱን የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ከ260 በላይ የሚሆኑ የውጭ ባለሃብቶች በተፈቀዱ የወጪ፣ ገቢ፣ ጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ ሥራዎች ለመሳተፍ ፍላጎት አሳይተዋል ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የ9 ወራት አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት አስታውቋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ የ78ቱ ፕሮፖዛል ተቀባይነት እንዳገኘና እስካሁን 40 የውጭ ባለሃብቶች ኢንቨስትመንት ፈቃድ ማውጣት እንደቻሉ ተገልጿል፡፡
የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ አለው ያለው ኮሚሽኑ፤ ኢትዮጵያ ካካሄደችው ሪፎርም አንፃር ከዚህ በላይ መሥራት ይገባል ብሏል፡፡
@sputnik_ethiopia