በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታማሚ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት የድጋፍ ዝግጅት አካሄደ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታማሚ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት የድጋፍ ዝግጅት አካሄደ
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታማሚ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት የድጋፍ ዝግጅት አካሄደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.04.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታማሚ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት የድጋፍ ዝግጅት አካሄደ

ዝግጅቱን የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጊኒ ቴሬክሂን እና ባለቤታቸው ከተስፋ አዲስ የወላጆችና ሕጻናት ካንሰር ድርጀት እና የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ (አፍሮኮም) ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁት ተገልጿል፡፡ በፕሮግራሙ የባህል፣ ሙዚቃ እና የመሳሰሉ አዝናኝ ዝግጅቶች እንደነበሩ ታውቋል፡፡

“እነዚህን አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተስቦች የመጡ ልጆች እዚህ የጋበዝነው በመጀመሪያ ደረጃ በራሳቸው እንዲያምኑ ለማስቻልና ህመሙን ማሸነፍ እንዲችሉ ለማበረታታት ነው፡፡ በተጨማሪ ለጥቂት ግዜም ቢሆን ስለ ህመማቸው እንዳይስቡ ለማድረግ ነው” ሲሉ አምባሳደር ኢቭጊኒ ቴሬክሂን ለስፑትኒክ ዘጋቢ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ ዝግጀቱ መጪውን የፋሲካ በዓል አስምልክቶ እንደተካሄደም ጠቁመዋል።

“ከመጪው የፋሲካ በዓል ጋር በተያያዘ የተካሄደ ነው፡፡ በሁለቱ ሀገራት የክርስትና እምነት ተከታዮች የፋሲካ በዓል ትልቅ ዓውድ ዓመት እንደመሆኑ ሕጻናቱ እንዲዝናኑ፣ በበዓሉ ቀን ደስታን እንዲያገኙ ለማገዝ ነው” ሲሉም አምባሳደሩ አክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ ዲፕሎማሲ መሪ መጪውን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

“ችግሮቻችንን እንደምናልፍ ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ የሁለቱም ሀገር ሕዝቦች ፋሲካን ደማቅ ፋሲካ የሚሉት ያለምክንያት አይደለም፡፡ እለቱ ተስፋችን የሚታደስበት፣ ጥንካሬ የምናገኝበት እና ለመጪው ግዜ ተስፋ የምንሰንቀበት ነው፡፡ ለሁሉም ኢትዮጵያወያን ክርስትያኖች፣ ሙስሊሞች እና ለሌሎች የእምነት ተከታዮች ሰላም፣ ብልጽግና፣ ጤና እና ፍቅር እመኛለሁ” ብለዋል፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታማሚ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት የድጋፍ ዝግጅት አካሄደ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታማሚ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት የድጋፍ ዝግጅት አካሄደ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታማሚ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት የድጋፍ ዝግጅት አካሄደ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0