አሜሪካ በውጭ የሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ ኢምባሲዎቿን ለመዝጋት ማቀዷ ተሰማ

አሜሪካ በውጭ የሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ ኢምባሲዎቿን ለመዝጋት ማቀዷ ተሰማ
"የትራምፕ አስተዳደር 10 ኤምባሲዎችን እና 17 ቆንስላዎችን ለመዝጋት እንዲሁም በርካታ ሌሎች የውጭ ተልዕኮዎችን እንዲሁም ሰራተኞችን የመቀነስ ወይም የማዋሃድ እቅዶችን እያጤነ ነው" ሲል የአሜሪካ ሚዲያ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሚስጢራዊ ሰነዶች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ሪፖርቱ በእቅዱ መሠረት አሜሪካ "በሁሉም አህጉራት" እንቅስቃሴዋን እንደምትቀንስ አመልክቷል።
በአፍሪካ እንደሚዘጉ የሚጠበቁ ስድስት የአሜሪካ ኤምባሲዎች፡-
🟠 ደቡብ አፍሪካ
🟠 ኤርትራ
🟠 ጋምቢያ
🟠 ሌሶቶ
🟠 ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
🟠 ደቡብ ሱዳን
"ሰነዱ በሞቃዲሾ ሶማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ወይም ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት መታቀዱን" ይጠቁማል።
በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚጠበቁ ለውጦች፡-
🟠 በሉክሰምበርግ እና ማልታ የሚገኙ የአሜሪካ ኢምባሲዎች ሊነኩ ይችላሉ።
🟠 በግሬናዳ እና በማልዲቭስ የሚገኙ የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች ይዘጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
🟠 በፈረንሳይ አምስት፣ በጀርመን ሁለት እና በቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና ሁለት ቆንስላዎቸ ሊዘጉ ይችላሉ።
🟠 በግሪክ፣ ጣሊያን እና ፖርቱጋል የሚገኙ በርካታ ሌሎች የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች የመዘጋት እጣ ፈንታ ሊገጥማቸው ይችላል።
🟠 በርካታ ቆንስላዎች ባሏቸው እንደ ጃፓን እና ካናዳ ባሉ ሀገራት የቆንስላ ድጋፍ በአንድ ቦታ ሊዋሃዱ ይችላሉ።
@sputnik_ethiopia