የኢትዮጵያ ልዑክ አረንጓዴ የኃይል ተነሳሽነቶችን ማፋጥን ላይ ያለመ ጉብኝት በህንድ እያደረገ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ልዑክ አረንጓዴ የኃይል ተነሳሽነቶችን ማፋጥን ላይ ያለመ ጉብኝት በህንድ እያደረገ ነው
የኢትዮጵያ ልዑክ አረንጓዴ የኃይል ተነሳሽነቶችን ማፋጥን ላይ ያለመ ጉብኝት በህንድ እያደረገ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.04.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ልዑክ አረንጓዴ የኃይል ተነሳሽነቶችን ማፋጥን ላይ ያለመ ጉብኝት በህንድ እያደረገ ነው

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለሙያዎች የተመራ ልዑክ ህንድ በታዳሽ ኃይል እና ዘላቂ የምርት ዘርፍ ላይ ያዳበረችውን ልምድ ለመቅሰም ኒው ዴልሂ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ጉብኝቱ ሁለቱ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የኢንዱስትሪ እድገት ለመፍጠር የሚያደርጉት ትብብር እየጨመረ እንደመጣ አመላካች ነው ሲል ኒው ዴልሂ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

"ይህ ከህንድ ጋር የሚደረግ ትብብር አረንጓዴ የኃይል ተነሳሽነቶችን ተቋማዊ ለማድረግ እና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልምዶችን ለማዳበር ወሳኝ ነው" ሲሉ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ተናግረዋል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0