ቅኝ ገዢዎች ለባርያ ስራዓት ካሳ የሚከፍሉበት "ወሳኝ ምዕራፍ" ላይ እንገኛለን ሲሉ የካሪቢያን ማሕበረሰብ ባለስልጣን ተናገሩ
14:43 16.04.2025 (የተሻሻለ: 14:54 16.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቅኝ ገዢዎች ለባርያ ስራዓት ካሳ የሚከፍሉበት "ወሳኝ ምዕራፍ" ላይ እንገኛለን ሲሉ የካሪቢያን ማሕበረሰብ ባለስልጣን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቅኝ ገዢዎች ለባርያ ስራዓት ካሳ የሚከፍሉበት "ወሳኝ ምዕራፍ" ላይ እንገኛለን ሲሉ የካሪቢያን ማሕበረሰብ ባለስልጣን ተናገሩ
የካሪቢያን ማህበረሰብ (ካሪኮም) ተወካይ የሆኑት ሂላሪ ብራውን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር የባርነት ካሳ ጥያቄ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ እና የቀድሞ ቅኝ ገዥ ሀገራት ተጠያቂ እንዲሆኑ ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠይቀዋል።
ብራውን በካሪኮም እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል እየተጠናከር የመጣው ትብብር የካሳ ክፍያ እንቅስቃሴው ወጥ ድምጽ እንዲኖረው አድርጓል ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውይይት በማድረግ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በሌሎች የባለብዙ ወገን ድርጅቶች በካሳ ዙሪያ የጋራ አቋም መያዝ እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡
"ካሪኮም ይህንን አጀንዳ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ዝግጁ ነው፡፡ አውሮፓን ተጠያቂ ለማድረግ ሃሳቡን ከሚጋሩ እና ቁርጠኝነቱ ካላቸው የአፍሪካ ሕብረት እና ሌሎች ጥምረቶች በጋራ ለመሥራት ዝግጁ ነን" ሲሉ ብራውን አክለዋል።
@sputnik_ethiopia