የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ አዲስ አብዮት ሊፈጥር ይችላል ያለውን የ3D ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ሀገር ውስጥ ላስገባ ነው አለ
11:57 16.04.2025 (የተሻሻለ: 12:14 16.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ አዲስ አብዮት ሊፈጥር ይችላል ያለውን የ3D ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ሀገር ውስጥ ላስገባ ነው አለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ አዲስ አብዮት ሊፈጥር ይችላል ያለውን የ3D ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ሀገር ውስጥ ላስገባ ነው አለ
ኮርፖሬሽኑ ቴክኖሎጂውን ወደ ሀገር ለማስገባት በዘርፉ ከሚሠራው የኦስትሪያው የግንባታ ቴክኖሎጂ አቅራቢ ባውሚት ግሩፕ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል በኦስትሪያ ከኩባንያው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ቴክኖሎጂወን ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡
ባውሚት ግሩፕ ቴክኖሎጂውን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስጀመር የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍና በትብብር እንደሚሠራ ኮርፖሬሽኑ በማህበራዊ ሚዲያ ባጋራው መረጃ ጠቁሟል፡፡
ቴክኖሎጂው 98 በመቶ የሚሆነውን ግብዓት ከሀገር ውስጥ የሚጠቀም ሲሆን ግዙፍ የመኖሪያ ቤት ግንባታዎችንና የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን በወራት እድሜ ለማጠናቀቅ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ