ጋና የውጭ ዜጎችን ከሀገር ውስጥ የወርቅ ገበያ አገደች
20:25 15.04.2025 (የተሻሻለ: 20:44 15.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጋና የውጭ ዜጎችን ከሀገር ውስጥ የወርቅ ገበያ አገደች
የጋና የወርቅ ቦርድ (ጎልድቦድ) ከሚያዝያ 23 ጀምሮ የአነስተኛ ደረጃ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮን ይቆጣጠራል።
የውጭ ዜጎች ከሚያዝያ 22 በኋላ ከወርቅ ንግድ ገበያ መውጣት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ወርቅን በቀጥታ መግዛት የሚችሉት ለጎልድቦድ በማመልከት ነው።
እርምጃው መንግሥት የሀገሪቱን ገንዘብ ለማረጋጋት እና የውጭ ምንዛሪ ክምችትን ለመጨመር የሚያደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ታምኗል።
ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ ጎልድቦድን በማቋቋም እና የውጭ ሀገር የወርቅ ዝውውርን በማገድ ኢንዱስትሪውን ለመቆጣጠር የገቡትን ቃል ለመጠበቅ የወሰዱት የመጀመሪያው እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።