የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በሩዋንዳ እያደረጉ ነው
17:16 15.04.2025 (የተሻሻለ: 17:34 15.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ወታደራዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በሩዋንዳ እያደረጉ ነው
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሩዋንዳ የመከላከያ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጄኔራል ሙባረክ ሙጋንጋ ጋር ውይይት አካሂደዋል።
“ጉብኝቱ በወታደራዊ መሪዎቹ መካከል በመከላከያ እና በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች ትብብርን ለማስፋትና አዳዲስ መስኮችን በመዳሰስ የረዥም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ቁልፍ ዕድል ይፈጥራል” ሲል የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር እና የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል።
ጄኔራል ሙጋንጋ በመጋቢት ወር አጋማሽ ኢትዮጵያን መጎበኝታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በአራት ቀን ቆይታቸው የ1994ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ተጎጂዎች መታሰቢያን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኒው ታይምስ የዜና ማሰራጫ ዘግቧል።