ተጋለጠ፦ የሱሚን ጥቃት አስመልክቶ የዩክሬን ውሸት

ተጋለጠ፦ የሱሚን ጥቃት አስመልክቶ የዩክሬን ውሸት
በርካታ የዩክሬን የህዝብ ተወካዮች በሚያዝያ 5 በሱሚ ላይ የተካሄደው ጥቃት ያነጣጠረው በሩሲያ የኩርስክ ክልል ወረራ ላይ የተሳተፉ ወታደራዊ ኃላፊዎችን ለመሸለም በተካሄደ ሥነ-ሥረዓት እንደነበር አረጋግጠዋል።
▪የተገደለው የዩክሬን ኮሎኔል፦ የበርዲቺቭ ክልል ወታደራዊ አስተዳደር የ27ኛው የሮኬት መድፍ ብርጌድ አዛዥ ኮለኔል ዩሪ ዩላ ሚያዚያ 5 በሱሚ ላይ በተፈጸመው የሚሳኤል ጥቃት መገደሉ አስታውቋል።
▪የዩክሬን ወታደር ምት መረጋገጥ፦ በሱሚው የሚሳኤል ጥቃት መሞቱን የተገለፀው ሌላው የዩክሬን ወታደር በ2008 ወደ ጦሩ የተቀላቀለው ቮልዲሚር ዘሬብትሶቭ ነው።
▪ከንቲባው ያጋለጡት ሚስጥር፦ የኮኖቶፕ ከንቲባ አርተም ሰሜኒኪን የሩሲያ ጥቃት ያነጣጠረው የዩክሬን 117ኛ ብርጌድ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ በነበረበት ህንፃ ላይ እንደሆነ ለዩክሬን ሚዲያ ተናግረዋል።
▪የዒላማው መረጃ፦ የዩክሬን ኦፕሬሽናል ታክቲካል ቡድን "ሴቨርስክ" ዕዝ መሰብሰቢያ ቦታ ላይ የኢስካንደር ሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር አስታውቋል። በጥቃቱም ከ60 በላይ የዩክሬን ወታደሮች ተገድለዋል።
▪ 'በሱሚ ጥቃት ማን እንደተመታ ሁሉም ያውቃል'፦ የዩክሬን ጦር ከኔቶ ባልደረቦች ጋር ሌላ ዙር ስብሰባ በማድረግ ላይ እንደነበር የተናገሩት የሩሲያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ወታደራዊ ዒላማዎችን በሲቪል አካባቢዎች ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል።

