ሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤል ፋሽር ሽብር እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ስትል ከሰሰች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤል ፋሽር ሽብር እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ስትል ከሰሰች
ሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤል ፋሽር ሽብር እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ስትል ከሰሰች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2025
ሰብስክራይብ

ሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤል ፋሽር ሽብር እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ስትል ከሰሰች

የሱዳን ባለሥልጣናት የአርኤስኤፍ ወታደሮች በቅርቡ በዛምዛም፣ አቡ ሹክ እና ኤል-ፋሽር በሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ካምፖች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት 450 ሲቪሎች ህፃናትን እና ሴቶችን ጨምሮ መገደላቸውን ተናግረዋል።

መንግሥት ጥቃቱ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት 2736 ውሳኔን እንደሚጥስና ዓለም አቀፋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርኤስኤፍ አሸባሪ ቡድን ተብሎ እንዲፈረጅ እና ለቡድኑ ወታደራዊ መሳሪያ የሚያቀርቡ አካላት ተጠያቂ እንዲደረጉ ጠይቋል።

የሱዳን መንግሥት ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር የአርኤፍኤስን የኤል-ፋሽር ወረራ ለመስበር፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለማስገባት እና ሲቪሎችን ለመጠበቅ ቃል ገብቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0