ኢትዮጵያ ቤላሩስ በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ ለምታደርገው ድጋፍና ለምታሳየው ገለልተኛ አቋም ምስጋና አቀረበች
17:20 14.04.2025 (የተሻሻለ: 17:34 14.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ቤላሩስ በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ ለምታደርገው ድጋፍና ለምታሳየው ገለልተኛ አቋም ምስጋና አቀረበች
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ከቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ራይዠንኮቭ ጋር በዛሬው እለት ውይይት አክሂደዋል፡፡
ውይይቱ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ በመሥራት የኢትዮጵያና የቤላሩስን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደነበር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስትር በለጠ ሞላ ሚንስክ በባለብዙ ወገን መድረኮች ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥልም ጠይቀዋል።
የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው በቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በማዕድን፣ በንግድ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል፡፡